የምንዛሬ ፓሊሲ ለውጡና የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ

ፋይል - ሴቶች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በልብስ ስፌት ፋብሪካ ውስጥ ሲሰሩ

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ በገበያው እንዲወሰን የፖሊሲ ለውጥ ካደረገ አንድ ወር ሁኖታል፡፡ ማሻሽያውን ተከትሎ ከቀደመው ጊዜ በተሻለ የውጭ ምንዛሬ ከባንኮች እያገኙ መሆኑን የተናገሩት የአሜሪካ ድምጽ ያናገራቸው በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብት በዘላቂነቱ ላይ ግን ስጋት አላቸው፡፡ እስካሁንም በፖሊሲ ለውጡ ምክንያት የደረሰባቸው ጉዳት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የምንዛሬ ፓሊሲ ለውጡና የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር አረጋ ሹመቴ በበኩላቸው ባለሃብቶቹ ለምርት ማቀነባበር የሚሆኑ ምርቶችን ቀደም ሲል ከውጭ የሚያስገቡት በጥቁር ገበያ ዋጋ እንደነበረ በመጥቀስ አሁን ባለው ዋጋ ብዙም ላይጎዱ ይችላሉ ይላሉ:;

ነገር ግን የምንዛሬ ዋጋው ከዚህ በላይ ካሻቀበ ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚሸጡበትና ለምርት ከውጭ የሚያስገቡት እቃ ዋጋ ልዩነት ስለሚራራቅ ምርታማ ሁነው ለመቀጠል መቸገራቸው አይቀርም ይላሉ::

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡