በአሰቃዊ ሁኔታ ተደፍራ ለተገደለችው ህጻን ሄቨን አወት የተለያዩ አካላት ፍትህ መጠየቃቸውን የቀጠሉ ሲሆን አርብ እለት አዲስ አበባ በሚገኘው ኢሊሌ ሆቴል ሊደረግ የነበረው እና በጸጥታ አካላት እንዲቋረጥ የተደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር በድጋሚ ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ ነው። የእናቶች ወግ ስለልጆች አስተዳደግ እና አመጋገብ የተሰኘው እና በፌስቡክ ላይ ከግማሽ ሚሊየን በላይ አባላት ያሉት ቡድን ቅዳሜ እለት ባካሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይም "እናቶች እና ህፃናት የሚያስጠልላቸው ህግ ይፈልጋሉ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
(ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ታገኛላችሁ)