የኤምፖክስ ፈንጣጣ ቅድመ መከላከል በኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

የኤምፖክስ ፈንጣጣ ቅድመ መከላከል በኢትዮጵያ

የዓለም ጤና ድርጅት ከዚህ ቀደም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተብሎ ይጠራ የነበረው የኤምፖክስ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ መሆኑን ከአንድ ሳምንት በፊት አስታውቋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ወረርሺኙ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ መጀመሩን አመልክቷል።

የኢኒስቲቲዩቱ ዋና ዲሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ፣ በሽታው ከተከሰተባቸው አገራት በሚመጡ ሰዎች ላይ የልየታ ስራ እየተደረገ እንደሚገኝ እና የበሽታው ምልክት እስካሁን በኢትዮጵያ እንዳልታየ ተናግረዋል፡፡