በአሜሪካ ምርጫ የትውልደ ኢትዮጵያ ድምጽ ሰጪዎች ዕይታ

Your browser doesn’t support HTML5

በአሜሪካ ምርጫ የትውልደ ኢትዮጵያ ድምጽ ሰጪዎች ዕይታ

ለአራት ቀናት የተከናወነው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ብሔራዊ ጉባኤ ትላንት ሐሙስ ምሽት ተጠናቋል።

ፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስን ለፕሬዝደንትነት፣ የሜንሶታው አገረ ገዥ ቲም ዎልዝን ደግሞ ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ አቅርቧል።

የሪፐብሊካኑ ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ባለፈው ሐምሌ እንዲሁ ተከናውኗል። ዶናልድ ትረምፕንና ጄ ዲ ቫንስን ፓርቲውን ወክለው ለፕሬዝደንትነትና ለምክትል ፕሬዝደንትነት እንዲወዳደሩ አቅርቧል።

SEE ALSO: ካመላ ሄሪስ ለአሜሪካ ፕሬዝደንትነት በፓርቲው መታጫተቸውን በይፋ ተቀበሉ

ሁለቱ ወገኖች ዋይት ሃውስን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት የምርጫ ዘመቻቸውን አጡጡፈው የሚቀጥሉበት ወቅት ላይ እንገኛለን። የምርጫ ክርክሮችም ቀነ ቀጠሮ ተቆርጦላቸዋል።

የሁለቱንም ፓርቲዎች ጉባኤ እና የዘመቻ አካሄድ በተመለከተ በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ያስባሉ?

ባልደረባችን እንግዱ ወልዴ የሁለቱም ፓርቲዎች ደጋፊ የሆኑ ድምፅ ሰጪ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አነጋግሮ ተከታዩን አዘጋጅቷል።