ሶማሊያ ‘ሉዓላዊነቴን ይጥሳል’ በሚል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ክልሏ እንዲበር እንደማትፈቅድ አስጠነቀቀች

ፋይል፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው 787 ድሪምላይነር አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊነሳ በዝግጅት ላይ።

የሶማሊያ መንግስት “የሉዓላዊነት ጥሰት” ስጋት ነው ያለውን ከበረራ መዳረሻ ጋር የተዛመደ ጉዳይ እስካልተፈታ ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሶማሊያ የሚያደርገውን በረራ ሊያስቆም እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሰጠው መግለጫ ከዚህ ቀደም ብሎ፣ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 14 አንስቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የደብዳቤ ልውውጥ ማድረጉን አመልክቷል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሶማሊያ ‘ሉዓላዊነቴን ይጥሳል’ በሚል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ክልሏ እንዲበር እንደማትፈቅድ አስጠነቀቀች።