በዴሞክራቲክ ፓርቲው ጉባዔ ሶስተኛ ቀን ውሎ፣ ፓርቲውን በመወከል የምክትል ፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩት ቲም ዋልዝ በይፋ ዕጩነታቸውን ተቀብለዋል። ከታዳሚው የጋለ ምላሽ ባገኘ ንግግራቸው፣ ከወታደርነት እስከ ግዛት አስተዳዳሪነት የተሻገረ ሙያዊ ጉዟቸውን አጋርተዋል። ለፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩት አጋራቸው ካማላ ኻሪስ አስተዳደር ለሀገሪቱ ህዝቦች ሊያመጣ የሚችለውን መልካም ውጤት ለማስረዳትም ጥረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኦፕራ ዊንፈሬይን የመሰሉ ታዋቂ ሰዎች ለካማላ ኻሪስ ድጋፍ ሰጥተዋል። ለመምረጥ ያልወሰኑ አሜሪካዊያን ድምጻቸውን ለመስጠት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቀርበዋል።
ጉባዔው በሚደረግበት ቺካጎ ከተማ የሚገኘው ሀብታሙ ስዩም ፣በዚያ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አስተያየት አክሎ ተጨማሪ መረጃዎች ያጋራናል ።