የዴሞክራቲክ ፓርቲ ወኪሎች እና የመጪው ምርጫ ፉክክር

Your browser doesn’t support HTML5

የዴሞክራቲክ ፓርቲ ወኪሎች እና የመጪው ምርጫ ፉክክር

የዴሞክራቲክ ፓርቲው ብሔራዊ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን ጨምሮ የፓርቲው አንጋፋ እና ወጣት ፖለቲከኞች ንግግሮችን አሰምተዋል። የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች፣ የፓርቲው ዕጩ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪ የሆኑትን ካማላ ሀሪስን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። ጉባዔው በሚደረግበት ስፍራ የተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው ወኪሎች ጆ ባይደን ከዕጩ ተወዳዳሪነት ለመነሳት መወሰናቸውን አድንቀው የም/ፕሬዚደንት ካማላ ሀሪስን ባለ አደራነት መቀበላቸውን በይፋ አሳይተዋል።

ቺካጎ የሚገኘው ባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን አጋርቷል።