ሩሲያ የባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ኪየቭ ተኮሰች

አንድ ሰው ከኪየቭ፣ ዩክሬን ወጣ ብሎ በራሺያ ሚሳኤል በተመታ ጊዜ የታየውን እሳተ ገሞራ ፎቶ ሲያነሳ፣ነሐሴ 12 2016 ዓ.ም.

ሩሲያ ዛሬ በዚህ ወር ለሶስተኛ ጊዜ የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ማድረሷን ዩክሬን አስታውቃለች፡፡

ነገር ግን የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኞቹ ተመትተው ወድቀዋል ሲል የኬቭ ወታደራዊ አስተዳደር አስታወቋል።

የኪየቭ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት ሰርሂ ፖፕኮ በቴሌግራም የመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ ላይ እንደገለጡት ሩሲያውያን በሰሜን ኮሪያ የተሰሩ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ተጠቅመዋል ብለዋል፡፡

ዘገባውን ያጠናቀረው የሮይተርስ የዜና ወኪል የሚሳኤሎችን አይነት በራሱ እንዳላረጋገጠ ገልጿል፡፡

የዩክሬን አየር ሃይል አዛዥ ሌተናል ሚኮላ ኦሌሽቹክ እንዳሉት ኪየቭን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀምበር ከተተኮሱት ስምንት የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ከስምንት ሚሳኤሎች ደግሞ አምስቱ ማውደም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡