የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ልዑካኖቹን ወደ ካይሮ እንደሚልክ አስታወቀ 

የሱዳን ጦር አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ ቡርሀን

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት በካይሮ ከግብጽ እና አሜሪካ ሃላፊዎች ጋር እንዲወያዩ ልዑካኖቹን ነገ ሰኞ እንደሚልክ አስታውቋል፡፡

የ16 ወራት ጦርነትን ለማስቆም ያለመው የሰላም ድርድር የመሳተፍ ጥያቄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በጅዳ የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ እስካልተደረገ ድረስ በስዊዘርላንድ በሚደረገው የሰላም ድርድር ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ በተመራውና በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም ታልሞ በሲውዘርላንድ ጄኔቭ በተዘጋጀው ድርድር በጄኔራል ሃምዳን ደጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሹ ጦር ልዑካኑን የላከ ቢሆንም በጄኔራል አልቡርሃን የሚመራው ወታደራዊ መንግስት አለመሳተፉን አስታውቋል፡፡

የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ልዑካኑን ወደ ካይሮ ለመላክ የወሰነው ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ እና ከግብፅ መንግስት ጋር ከተነጋገረ በኋላ መሆኑን አስታውቋል፡፡