ብሊንከን ወደ እስራኤል ይጓዛሉ 

ፋይል፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንበዶሃ፣ ኳታር ለመነሳት በአውሮፕላኑ ላይ ሲሳፈሩ፣ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. (Ibraheem Al Omari/Pool Photo via AP)

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አንተኒ ብሊንከን በጋዛ የተኩስ አቁም በሚደረግበት ጉዳይ ላይ ለመምከር ዛሬ እሁድ እስራኤል ይገባሉ ተብሎ ተጠብቋል፡፡

ይህ ጉዟቸውም በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ላለፉት 10 ወራት የዘለቀው ጦርነት እንዲያበቃ የሚያስችል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ዋሽንግተን እያደረገችው ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግፊት አካል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ብሊንከን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ወደ አካባቢው ያደረጉት አስረኛ ጉዟቸውም ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልና ሃማስን ሊያስማሙ ይችላሉ ያለችውን የድርድር ሃሳቦች ባቀረበችበትና ግብጽና ኳታር ሃሳቡ በተፋላሚዎች መካከል ያሉ ልዩነትቶችን ለማጥብብ ያስችላል ብለው ተስፋ ባደረጉ ማግስት የተደረገ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴት ባለስልጣናትም በድርድሩ ውጤታማነት ላይ አዲስ ተስፋ ያሳዩ ቢሆንም አሁንም ግን ጥንቃቄዎችን የሚፈልጉ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ እየተናገሩ ይገኛል፡፡

ብሊንከን በእስራኤል ጉዟቸው ከጠቅላይሚንስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁና ሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋርም ይመክራሉ ተብሏል፡፡