መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውሳኔውን እንዲሰርዝ ኢሕአፓ ጠየቀ

“አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ወቅት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ያስከትላል፤” ሲል ስጋቱን የገለጸው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ኢሕአፓ/፣ መንግሥት የፖሊሲ ለውጥ ውሳኔውን እንዲሰርዝ ጠየቀ፡፡

የኢሕአፓ ሊቀ መንበር አቶ ዝናቡ አበራ፣ “ምርታማነትን ጎድተዋል” ያሏቸው “የሰላም ዕጦት እና ሕገ መንግሥቱ”፣ “የማሻሻል ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር፤” ብለዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውሳኔውን እንዲሰርዝ ኢሕአፓ ጠየቀ

የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያው “የግድ አስፈላጊ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ለውጤታማነቱ ሰላም የግድ አስፈላጊ እንደኾነና ለዚህም ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በተያያዘ፣ የውጭ ምንዛሬ በገበያ እንዲመራ ከመወሰኑ ጋራ ተያይዞ፣ የኢትዮዽያ አየር መንገድ የአውሮኘላን ቲኬት ዋጋ ላይ “ከፍተኛ ጭማሬ አድርጓል” በሚል ለሚቀርቡ አስተያየቶች፣ አየር መንገዱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት መምህር የኾኑት ዶክተር ዳኪቶ ዓለሙ፣ የሰጡንን አስተያየት ያካተተውን የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡