የወላይታ ዞን 53 አባወራዎችን ለመሬት መንሸራተት ከሚያሰጋ ስፍራ ማውጣቱን ገለጸ

በካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ የደረሰው የመሬት መናድ (ፎቶ: የወላይታ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ 08/05/2024)

ትላንት ሰኞ፣ 11 ሰዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ከሞቱበት የወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ተጨማሪ ጉዳትን ለመከላከል፣ 53 አባወራዎች ከቀዬው እንዲወጡ ማድረጉን፣ የዞኑ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ከአደጋው ክሥተት ሦስት ቀናት በፊት መሬቱ ተሠንጥቆ እንደነበረ ያወሱት የተጎጂ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች፣ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤት ውስጥ መጠለላቸውን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የወላይታ ዞን 53 አባወራዎችን ለመሬት መንሸራተት ከሚያሰጋ ስፍራ ማውጣቱን ገለጸ