ላለፉት ሦስት ቀናት፣ በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ተቀስቅሶባት የነበረችው የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ታቦር፣ ዛሬ ወደ አንጻራዊ መረጋጋት መመለሷን፣ ነዋሪዎች እና የአካባቢ አስተዳደር ገልጸዋል፡፡
በግጭቱ ተዘግተው የቆዩ የንግድ ተቋማት እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም መከፈታቸውን፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በከተማው ግጭት እንደነበር፣ ትላንት ሰኞ፣ በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ ያረጋገጠው የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር፣ “በተሳሳተ መንገድ ለተሰለፉ” ሲል የጠራቸው አካላት ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5