ዩክሬን በማሊው ጥቃት እጄ የለበትም አለች 

ፋይል - በማሊ በአዛዋድ ክልል ውስጥ የቱዋሬግ የፖለቲካ እና የታጣቂዎች ንቅናቄ መኪና ላይ የፀረ-አውሮፕላን የጦር መሳርያ ተጭኖ ይታያል፣ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.

ዩክሬን ለማሊ ወታደሮች እና ዋግነር ተዋጊዎች ሞት ምክንያት በሆነው በሰሜን ማሊው የሀምሌ ወር ጦርነት ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌላት ገለጸች፡፡

ማሊ ድርጊቱን ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ለማቋረጥ መወሰኗ “የጥድፊያ ርምጃ እና አጭር እይታ” ነው ብላለች፡፡

ማሊ ትላንት እሁድ ባወጣቸው መግለጫ ከዩክሬን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነኝ ማቋረጧን አስታውቃለች

ማሊ አቋማን የገለጸችው የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ አንድሪ ዩሶቭ የማሊ አማፂያን ጥቃቱን ለመፈፀም "አስፈላጊ" መረጃ እንደደረሳቸው ለሰጡት አስተያየት ምላሽ ነው፡፡

ዩሶቭ ሀምሌ 29 በሰጡት አስተያየት ኪቭ በግጭቱ ውስጥ መሳተፏን በቀጥታ አላረጋገጡም።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማሊ የሽግግር መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ ማዘኑን የገለፀ ሲሆን፥ የተፈፀመውን አደጋ፣ እውነታ እና ሁኔታ በጥልቀት ሳይጠና የተወሰደ ውሳኔ ነው ብሏል።

"ዩክሬን የዓለም አቀፍ ህግና ደንቦችን የሌሎች ሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነትን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ታከብራለች" ሲል መግለጫው አመልከቷል፡፡