መንግሥት ከፋኖ ጋራ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ 

ጠቅላይሚንስትር ዐቢይ አህመድ ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. (Photo - Prime minster office of Ethiopia)

መንግሥታቸው፣ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ በምስጢር ንግግር ማድረግ መጀመሩን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት በትላንቱ መድረክ ላይ ይህን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በንግግሩ መሀል ሦስተኛ ወገን ይኑር አይኑር ግን አልገለጹም።

በአቶ ዘመነ ካሴ ይመራል ባሉት የአማራ ፋኖ፣ በጎጃም የውጭ ጉዳይና የዲያስፖራ ጉዳዮች መምያ ኃላፊ መኾናቸውን የገለፁልን አቶ ስሜነህ ሙላቱ ከመንግሥት ጋራ ምንም የተጀመረ ንግግርም ሆነ ድርድር እንደሌላ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

መንግሥት ከፋኖ ጋራ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ 

የዐማራ ክልል የሰላም ካውንስል ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ በበኩላቸው፣ ይፋዊ ንግግር ስለመጀመሩ እንደማያውቁ ገልጸው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግን፣ “የፌዴራሉ መንግሥት ጥሪያችንን መቀበሉን የሚያመለክት ነው፤” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሸኔ” ሲሉ ከጠሩት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋራም ምስጢራዊ ንግግር እየተደረገ ነው፤ ብለዋል።

ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ።