የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናት፣ ዐዲስ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መከሠቱን ከዐወጁ በኋላ፣ ምንጩን ለማጣራትና የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ፣ ከጎረቤት ሀገራት መንግሥታት ጋራ ተገናኝተው መምከራቸውን ተናግረዋል።
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ለበሽታው እንደተጋለጡ የተጠረጠሩ ከ12ሺሕ በላይ ሰዎች መኖራቸውን ባለሥልጣናቱ ገልጸው፣ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ወደ 500 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ በሽታው ሊስፋፋ እንደሚችል መገመቱም አሳስቧቸዋል፡፡
ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜካ ከያውንዴ-ካሜሩን ያዘጋጀው ዘገባ ይከታተሉ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5