አፍጋንስታን በውጭ ሃገራት ያሏትን በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች እና ‘በምዕራባውያን ይደገፍ ከነበረው የቀድሞው የአገሪቱ መንግስት ጋር ግንኙነት ባላቸው ዲፕሎማቶች የተሰጡ’ ፓስፖርቶች፣ ቪዛ እና ሌሎች ሰነዶች አልቀበልም’ ሲል አብዛኛውን ውድቅ ማድረጉን አስታወቀ።
ይህም ታሊባን የአገሪቱን የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ለመቆጣጠር ያደረገው የቅርብ ጊዜው ሙከራ ተደርጎ ተወስዷል። በውጪ አገራት ያሉ አንዳንድ አፍጋናውያንም ‘ኢፍትሃዊ እና ተግባራዊነት የጎደለው’ ሲሉ ቡድኑ የወሰደውን እርምጃ ተቃውመዋል።
የአፍጋንስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፡ ‘ለንደን፣ በርሊን፣ ቤልጂየም፣ ቦን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ግሪክ፣ ፖላንድ፣ አውስትራሊያ፣ ስዊድን፣ ካናዳ እና ኖርዌይ በሚገኙት የሃገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የተሰጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም’ ብሏል።
የሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ አክሎም ‘እዚያ የሚገኙት ሰዎች በምትኩ የታሊባን እስላማዊ የአፍጋን መንግስት የሚቆጣጠራቸውን ኤምባሲዎችን እና ቆንስላዎች ማነጋገር አለባቸው’ ብሏል።