በሲዳማ ክልል የመሬት መንሸራተት አደጋ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያን የሚያሳይ የሳተላይት የካርታ ምስል

በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ቀበሌ በተከሠተ የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ 11 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምዖን፣ ትላንት እሑድ ምሽት የጣለው ከባድ ዝናም አደጋውን ማስከተሉን ገልጸው፣ ከሞቱ ሰዎች በተጨማሪ በስድስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በሲዳማ ክልል የመሬት መንሸራተት አደጋ 11 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ