እንግሊዝ ውስጥ 8 ሰዎች በስለት ተወጉ

ፋይል፡ አንድ ሰው በብሪታንያ ሳውዝፖርት ፒየር ፊት ለፊት ባለው የባህር ዳርቻ ላይ በብረት መመርመርያ የተቀበረ ነገር ሲፈልግ ያሳያል፣ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም.

ዛሬ ሰኞ እንግሊዝ ውስጥ ቢያንስ ስምንት ሰዎች በስለት መዋጋታቸው ተነገረ፡፡

በሰሜን ምዕራብ እንግሊዝ ሳውዝፖርት ውስጥ በደረሰው ከዚህ አደጋ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል፡፡

በአካባቢው የሚገኝ የህጻናት ሆስፒታል ድርጊቱን ትልቅ አደጋ ሲል፣ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በጣም አስደንጋጭ ብለውታል፡፡

የሰሜን ምዕራብ አምቡላንስ አገልግሎት የአልደር ሄይ ህጻናት ሆስፒታልን ጨምሮ ወደ ሶስት የተለያዩ ሆስፒታሎች የተወሰዱ በስለት ተወግተው ለቆሰሉ ስምንት ሰዎች ህክምና መስጠት ችያለሁ ብሏል።

የመርሲሳይድ ፖሊስ እንደገለጸው ከቀኑ 11፡50 ላይ አደጋ መድረሱ በተገለጸበት ስፍራ ፖሊስ ቢላዋ መያዙ የተነገረውን አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የአደጋውን መንስኤ ዘገባው አላመለከተም፡፡