የመሬት ናዳ አደጋ ከደረሰበት ገዜ ጎፋ ወረዳ አምስት ሺሕ ነዋሪዎች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ከደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጋራ በተያያዘ፣ አምስት ሺሕ የሚደርሱ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

የወረዳው አደጋ ስጋት ሥራ አመራር በበኩሉ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ2ሺሕ500 በላይ ዜጎች መለየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የመሬት ናዳ አደጋ ከደረሰበት ገዜ ጎፋ ወረዳ አምስት ሺሕ ነዋሪዎች ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ

ለነፍስ ማዳን ሥራ ወደ ስፍራው ካቀኑት ውስጥ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር የኾኑት ዘለቀ ዶሳ፣ በአደጋው አምስት ዘመዶቻቸውን ማጣታቸውን ጠቅሰው፣ ኹኔታው “ልብ የሚሰብርና አሠቃቂ ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዥ፣ የተከሠተውን አደጋ ለመግለጽ የሚጨንቅ መኾኑን ጠቁመው፣ ስለ ጠፋው የሰው ሕይወት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡