የ2016 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ፣ ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተጓዙ ተማሪዎች፣ በጸጥታ ችግር ሳቢያ ከእንቅስቃሴ ታቅበው እንደሚገኙ የገለጹ የቤተሰብ አባላት፣ ልጆቻቸው እንዲመለሱላቸው ተማፅነዋል፡፡
ከፍቼ ወደ ደራ በሚወስደው መንገድ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የፋኖ ታጣቂ ኀይሎች እንደሚንቀሳቀሱ ጠቅሰው አስተማማኝ ትራንስፖርት አለመኖሩን ያመለከቱት የተማሪዎቹ ቤተሰቦች፣ ለፈተናውም ሲሔዱ በመከላከያ ታጅበው እንደነበር አስረድተዋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የተማሪዎች ቤተሰቦች ባሰሙት አቤቱታ ላይ ከደራ ወረዳ፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር፣ ከአኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ፣ ከትምህርት ሚኒሰቴር እና ከፈተናዎች ኤጄንሲ መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡