እስራኤል ዜጋዋ በሁቲ አማጺያን ጥቃት ከተገደለ ከሰዓታት በኃላ ከየመን የተተኮሰ ሚሳኤል መትታ ጣለች

በአውሮፓዊያኑ ሰኔ 14 የተነሳው ምስል በሰሜን እስራኤል ቂርያት ሽሞና አቅራቢያ ከደቡብ ሊባኖስ የተተኮሱትን ሮኬቶችን ለማምከን የተተኮሰ የእስራኤል አየር መከላከያ ስርዓት ሚሳይልን ያሳያል።


የእስራኤል ጦር ከየመን የተተኮሰ ሚሳኤል ዛሬ እሁድ አየር ላይ መማከኑን አስታወቀ ። ይህ የተሰማው የእስራኤል የጦር አውሮፕላን በአረቢያ ባሕረ ገብ መሬት ላይ የሚገኙ በርካታ የሁቲ ኢላማዎችን በደበደቡ በሰዓታት ውስጥ ነው ።

ሁቲዎች በቴላቪቭ ላይ ላደረሱት የሰው ህይወት ለቀጠፈ የድሮን ጥቃት አጸፋ የሆነው የአሁኑ እስራኤል የአየር ጥቃት ፣ እስራኤል ለዘጠኝ ወራት ያህል ከሀማስ ጋር ጦርነት በገባችበት ወቅት በተደጋጋሚ ለተሰነዘረባት የሁቲ ጥቃቶች የተሰጠ የመጀመሪያው ምላሽ ነው ።

በሩቅ ጠላቶች መካከል ብጥብጥ መፈንዳቱ ፣ እስራኤል በቀጠናው የኢራን ውክል ተዋጊዎችን የምትፋለምበት ሌላ አዲስ የፍልሚያ ግንባር እንዳይከፍት አስግቷል ። .

የእስራኤል ጦር ቅዳሜ ምሽት በምዕራብ የመን የሁቲዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነችው ሆዳይዳ የወደብ ከተማ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል ። ጦሩ በአሜሪካ ሰራሾቹ ኤፍ -15 እና ኤፍ -35 የጦር አውሮፕላኖች የፈጸመው ጥቃት በሆቲ አማጺያን ለተሰነዘሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶች አጸፋ መሆኑን አስታውቋል ።

እስራኤል ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ፣ ብሪታኒያ እና እና ሌሎች ምዕራባዊያን አጋሮች ጋር በመሆን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ የሁቲ ሚሳኤሎች እና ድሮኖችን ጉዳት ሳያደርሱ ማምከን ችለዋል ። ይሁንና አረብ ዕለት ማለዳ የእስራኤልን የአየር መከላከያ ጥሶ በንግድ እና ባህል ማዕከል መናገሻዎ ቴላቪቭ ያረፈ ድሮን አንድ ሰው ገድሏል።

እስራኤል ከድንበሯ 1700 ኪሜ ላይ በሚገኝ ስፍራ ላይ ቅዳሜ የፈጸመችው ጥቃት ፣ በአየር ጦሯ ከተፈጸሙ በእጅጉ ውስብስብ የረጅም ርቀት ዘመቻዎች አንዱ መሆኑን ጦሯ አስታውቋል ።ጦሩ ወደቡን የደበደበበት ምክንያት ስፍራው ኢራን ለየመን መሳሪያ የምታቀርበበት በመሆኑ እንደሆነ ጦሩ አክሏል።

በሰንኣ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር በሆዳይዳ ባደረገው በመጀመሪያ ዙር ቆጠራ 80 ሰዎች መጎዳታቸውን እንደደረሰበት አስታውቋል ። አብዛኞቹ በከፋ ሁኔታ በእሳት የመለብለብ አደጋ ገጥሟቸዋል ። የእስራኤል ጥቃት በወዳቧ ከተማ ከፍተኛ እሳት መቀስቀሱ ይታወሳል( ኤፒ) ።