በትራምፕ የግድያ ሙከራ ላይ የባለሞያዎች አስተያየት

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት እና የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ፣ ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በፔንሰልቬኒያ፣ ባትለር ውስጥ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጉበት ከነበረው መድረክ እንዲወርዱ በሰዎች ሲረዱ

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት እና የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ ወራቶች በቀረው የአሜሪካ ምርጫ የመራጮች ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ባለሞያዎች ገለጹ።

በተለያዩ የአሜሪካ ዩንቨርስቲዎች ያስተማሩትና በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እያስተማሩ የሚገኙት የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ይህ ዓይነቱ ክስተት በአሜሪካ የቀደሙ ታሪኮች ላይ ደጋግሞ የተስተዋለ ቢሆንም አሜሪካኖች እንደዚህ ዓይነት ክስተት በሚፈጠርበት ወቅት ወደ አንድነት የሚመጡበት ነው ይላሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

በትራምፕ የግድያ ሙከራ ላይ የባለሞያዎች አስተያየት

ክስተቱ በአሜሪካ ፖለቲካ ላይ ትልቅ መነጋገርያ በሆነው የጦር መሳርያ ባለቤትነት መብት ላይ ያሉ ክርክሮችን መነጋገርያ እንዲሆን የሚያስችል ነውም ይላሉ።

አሜሪካ ፖለቲካን በቅርበት እንደሚከታተል የሚገልጸው የፖለቲካል ተንታኝ አቶ ብስራት ከፈለኝ በበኩላቸው ክስተቱ በምርጫ ሂደቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ቢኖርም በተቋማት በተገነባው የአሜሪካ የፖለቲካ ስርዓት ላይ የሚፈጥረው ችግር እንደሌለ ይናገራሉ።