የአፍሪካ መከላከያ ባለሥልጣናት በቦትስዋና ሊመክሩ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ የዩኤስ አፍሪካ ዕዝ አርማ በሽቱትጋርት፣ ጀርመን፣ እአአ መስከረም 5/2019

ሠላሳ የአፍሪካ ሃገራትን የሚወክሉ የመከላከያ ሃላፊዎች አህጉሪቱ በገጠማት የፀጥታ እና የመረጋጋት ተግዳሮቶች ላይ ለመነጋገር በመጪው ሳምንት ቦትስዋና ላይ የሁለት ቀናት ጉባኤ ይቀመጣሉ። ጉባኤው የተዘጋጀው ‘አፍሪኮም’ በመባል የሚታወቀው የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ሲሆን፣ ተመሳሳይ ጉባኤ መካሄድ ከጀመረበት ከእ.አ.አ 2017 ወዲህ በአህጉሪቱ ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ መከላከያ ባለሥልጣናት በቦትስዋና ሊመክሩ ነው

ኮንዲሲ ዱቤ ከጋቦሮኔ የላከውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።