ለኪቭ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሳየት የአለም መሪዎች  በዩክሬን የመሪዎች ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ ሰኔ 2016

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ ሰኔ 2016

የአለም መሪዎች ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት እንድታቆም ጫና ለመፍጠር በስዊዘርላንድ የዩክሬን ጉባዔ ላይ ተሰባሰበዋል። ይሁን እንጂ እንደ ቻይና ያለች ሃያል የሞስኮ ደጋፊ በስፍራው አለመታደም የጥረቱን አቅም አደብዝዞታል።

ከአስር በላይ የሚሆኑ የዩክሬን አጋሮች በጉባዔው ላይ የሚታደሙ ቢሆንም፤ ቻይና ሩሲያ ከጉባዔው ከታገደች በኋላ ጉባዔው ጊዜ ማባከን ነው ስትል የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላት አስታውቃለች።

ይህን ተክትሎም ካለ ቻይና ሞስኮን የማግለል ተስፋ እየደበዘዘ መጥቷል። በተመሳሳይ በጋዛ እና በእስራኤል መካከል የሚደረገው ጦርነት ከዩክሬን ትኩረትን ማራቁም ተገልጿል።

ጉባዔው ጦርነቱን ተከትለው በመጡ የምግብ፣ የኒውክሌር ደህንነት እና የመንቀሳቀስ ነጻነት ችግሮች የሚታዩበት እንዲሁም ሩሲያ ግጭት ቆስቋሽ መሆኗ ለይቶ የሚያወጣ የመጨረሻ አዋጅ ረቂቅ የሚዘጋጁበት ሰፋ ባሉ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።