ኢራን እና ስዊድን ዛሬ ቅዳሜ የእስረኛ ልውውጥ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በስዊድን በጎሮጎርሳዊያኑ 1988 በእስላማዊ ሪፐብሊኩ የጦር ወንጀል እንዲፈጸም ታዟል በሚል የተከሰሰው ሃሚድ ኗሪ በቴህራን ይዞታ ስር በሚገኙ ሁለት እስረኞች ልውውጥ ወደ ኢራን እንደሚመለስ ተገልጿል።
በአንጻሩ ኢራን ለአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ልዑክ የሚሰራውን ጆሃን ፍሎዴረስ እና በስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዒድ አዚዝ ተብሎ ስሙ የተገለጸ ግለሰብን ለመልቀቅ ተስማማታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ማኅበራዊ መተግበሪያ ገጻቸው ላይ “እስረኞቹ ወደ ስዊድን በአውሮፕላን ጉዞ ማድረግ ጀምረዋል በቅርቡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይገናኛሉ” ሲሉ አስፍረዋል።
በኦማን መንግስት የሚመራ የመንግስት የዜና ጣቢያ ኦማን የእስረኛ ልውውጥ ድርድሩን መርታለች ማለቱን የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አስታውቋል። በተመሳሳይ የኢራን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ቴሊቪዥን ጣቢያ ኑሪ ተፈትቶ ወደ ቴህራን እየመጣ ነው ሲል ዘግቧል።
በጎርጎርሳዊያኑ 2022 የስቶክኾልም አውራጃ ፍ/ቤት ኑሪን የእድሜ ልክ እስራት በይኖበት ነበር።