የሩስያ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚንስትሮች የቻድ እና የሳህል ሀገሮች ጉብኝት

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

የሩስያ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚንስትሮች የቻድ እና የሳህል ሀገሮች ጉብኝት

ጊኒን እና የኮንጎ ሪፐብሊክን የጎበኙት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትላንት ረቡዕ ቻድን ጎብኝተዋል፡፡ የሩስያ የመከላከያ ሚንስትር ዩኑስ-ቤክ ዪቭኩሮቭ በበኩላቸው ሊቢያ እና ኒዠርን ጎብኝተዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች እና ተንታኞች የሩሲያ ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ጉብኝቶች ወታደራዊ መሪዎች ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ ወታደሮቿን ለማስገባት የምታደርገው እንቅስቃሴ አድርገው ይመለከቱታል፡፡

ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ፣ ኒዠር እና ቻድ ውስጥ የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ኅይሎች መገኘትን በሚመለከት ርዕዮተ ዓለማዊ ልዩነቶች መቀስቀሳቸውን አክሎ ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜጋ ከያውንዴ ዘገባ አስተላልፏል፡፡ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡