ዛሬ በጋዛ ደቡባዊ ከተማ ራፋህ ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ጦርነቱ የተቀሰቀሰው የእስራኤል ጦር የመጀመሪያዎቹ 310 ትላልቅ የሰብአዊ እርዳታ እሽጎች፣ አሜሪካ በገነባችው የባህር ዳርቻ ማራገፊያና ማስተላለፊያ በኩል ወደ ተከበበችው ግዛት ከገቡ በኋላ ነው፡፡
የእስራኤል ጦር በራፋህ “ውስን” ሲል በጠራውና ከ10 ቀናት በላይ ያስቆጠረው ወታደራዊ ዘመቻ፣ በእስራኤል ጦር እና በፍልስጤም ታጣቂዎች መካከል በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል እንደገና ጦርነት ተቀስቅሷል።
የኩዌት ሆስፒታል፣ እስራኤል በአንድ ጀምበር ባደረገችው ጥቃት በራፋህ በሚገኝ የተፈናቃይ ካምፕ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
በከተማዋ ደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ የተኩስ ጥቃት መፈጸሙን እና ጄቶች በምስራቃዊ ደቡብ አካባቢ ድብደባ እንደፈፀሙ እማኞች ተናግረዋል።
የእስራኤል ጦር ትላንት ዓርብ በከተማዋ ውስጥ የተካሄደው ጥቃት ከሰባት ወራት በላይ በዘለቀው ጦርነት “ምናልባትም እጅግ የከፋው” ነው ብሏል፡፡
በሰሜን ጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በአንድ ሌሊት የተካሂዱ ከባድ ውጊያዎች እንደነበሩ የዐይን ምስክሮች፣ የህክምና ባለሙያዎችና ዘጋቢዎቹ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ድርጊቱ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቢያጋጥመውም እስራኤል ራፋህ ላይ ጦርነት ጀምራለች፡፡
ሸምጋዮች የተቋረጠው የእርቅ ድርድር እመርታ እንደሚያሳይ ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ ቀድሞውንም አስከፊ የሆነውን ሰብአዊ ቀውስ እንዳባባሰው የእርዳታ ቡድኖች ገልጸዋል።