ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬሎች ሳይሆኑ እንዳልቀረ የሚገመቱ ሚሳዬሎችን ለሙከራ ዛሬ ሰኞ ማስወንጨፏን ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች፡፡
የጦር መሣሪያ ሙከራዋን በመቀጠል ላይ ያለችው ሰሜን ኮሪያ፣ የተከለከለ ሳተላይት ልታመጥቅ ትችላለች የሚለው ስጋትም በመጨመር ላይ ነው።
የደቡብ ኮሪያ ኤታማዦር ሹሞች ቡድን “ግልጽ ትንኮሳ” ሲል በመግለጽ ሙከራውን አውግዟል። ቡድኑ እንዳስታወቀው ሚሳዬሎቹ 300 ኪሎሜትር ከበረሩ በኋላ በጃፓን እና በኮሪያ ባሕረ ገብ መሬት መካከል በሚገኘው የውቅያኖስ አካል ላይ አርፏል። የርቀቱ መጠን ምናልባትም ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያን ኢላማ እንደምታደርግ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል።
ደቡብ ኮሪያ ከአሜሪካ ጋራ ባላት ወታደራዊ ቃል ኪዳን መሠረት ለትንኮሳው “ከበድ ያለ“ ብለው የገለጹትን የአጸፋ መልስ እንደምትሰጥ የኤታማዦር ሹሞቹ ቡድን አስታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ 250 ኪሎሜትር የተጓዘ ቢያንስ አንድ ባሊስቲክ ሚሳዬል አስወንጭፋለች ስትል ጃፓን በበኩሏ አስታውቃለች፡፡