በግጭት ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህጻናትን ከእኩዮቻቸው እኩል የሚያደርገው ተቋም

Your browser doesn’t support HTML5

በግጭት ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህጻናትን ከእኩዮቻቸው እኩል የሚያደርገው ተቋም

‘ዘ ሉሚኖስ ፈንድ’ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት እና በሶሪያ የሚንቀሳቀስ፤ በትምህርት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ገባሬ ሰናይ ተቋም ነው። ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጋምቤላ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎች ይንቀሳቀሳል።

ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከ300 ሺህ በላይ በግጭት በአየር ንብረት ለውጥ እና በኑሮ ውድነት ሳቢያ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ህጻናት በተፋጠነ የትምህርት መርሃግብር አማካኝነት፤ለአንድ ዓመት ያህል አስተምሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በመፈተን ከእድሜ እኩዮቻቸው እኩል ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ችሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በግጭት እና በሀገር ውስጥ መፈናቀሎች ምክንያት ለአዕምሮ ጠባሳ እና እንዲሁም ለድህረ አደጋ ሰቀቀን የተጋለጡ መምህራንን እና ተማሪዎችንም ያግዛል። ኤደን ገረመው የተቋሙን የምሥራቅ አፍሪካ ዲሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ኃይሉን እንዲሁም በትግራይ ክልል እና ድሬዳዋ ከተማ ያሉ እናቶችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።