የአየር ንብረት ለውጥን ላገናዘበ አኗኗር መዳበር የተማሪዎች ቁልፍ ሚና

Your browser doesn’t support HTML5

የአየር ንብረት ለውጥን ላገናዘበ አኗኗር መዳበር የተማሪዎች ቁልፍ ሚና

በ16 ዓመት አዳጊ ወጣት፣ ከሦስት ዓመት በፊት የተመሠረተው “የኢትዮጵያ የተፈጥሮ አፍቃርያን” የተሰኘ እንቅስቃሴ፣ በአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ፣ በ12 ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ግንዛቤ አስጨብጧል።

አሁን ደግሞ፣ ከዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ቀጣዩን ትውልድ፥ በአካባቢ ጥበቃ ትምህርት፣ በአረንጓዴ ልማት እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በማስተማር ተጽእኖ ለመፍጠር የሚያስችል እንቅስቃሴ ጀምሯል።

አዳጊዋ ልዕልና ኀይሉ እና የዋን ፕላኔት መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም አማረ፣ ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ የአየር ንብረት ለውጥን ያገናዘበ አኗኗር እንዲያዳብሩ ማገዝ ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ሐሳባቸውን አካፍለዋል። ያናገረቻቸው ስመኝሽ የቆየ ናት፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።