በመኾኒ ከተማ የተጠለሉ የአላማጣ ተፈናቃዮች ሰልፍ በመውጣት ለመመለስ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በመኾኒ ከተማ የተጠለሉ የአላማጣ ተፈናቃዮች ሰልፍ በመውጣት ለመመለስ ጠየቁ

ከአላማጣ እና አካባቢዋ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲተገበር የሚጠይቅ ሰልፍ በመኾኒ ከተማ አካሔዱ፡፡

የትግራይ እና የአማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸውና አወዛጋቢ በሚባሉ አካባቢዎች፣ ሰልፉን ተከትሎ፣ ከአማራ ክልል በኩል ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸውን ገልፀው የሰልፉ አስተባባሪዎች ክስ አሰምተዋል።

የአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ አቶ ኀይሉ አበራ፣ “አብዛኛው ተፈናቃይ ተመልሷል፤ ለመመለስ የሚፈልግና የቀረ ተፈናቃይ ካለም መመለስ ይችላል፤” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

አያይዘውም፣ “ተኩስ የከፈቱት የትግራይ ታጣቂዎች ናቸው፤” ሲሉ የሰልፉን አስተባባሪዎች ክስ አስተባብለዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።