ባንኩ የደንበኞቹን እምነት እና ዝናውን ለማስመለስ መሥራት ይኖርበታል ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

ባንኩ የደንበኞቹን እምነት እና ዝናውን ለማስመለስ መሥራት ይኖርበታል ተባለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከሦስት ሳምንት በፊት በድጅታል የግብይት ሥርዓቱ ላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ የተወሰደበትን ገንዘብ እያስመለሰ ይገኛል፡፡

ባንኩ በወቅቱ እንደተወሰደበት ከገለጸው ገንዘብ 86 በመቶውን ማስመለስ መቻሉን አስታውቋል፡፡ እስከ አሁን አላግባብ የወሰዱትን ብር አልመለሱም ያላቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር፣ ከፎቷቸውና የባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው ጋራ በይፋ እያሳወቀ ይገኛል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው የሕግ ባለሞያው አቶ ዳዊት ገብሩ፣ ባንኩ የሰዎችን ማንነት ይፋ ያደረገበት መንገድ ሕግን ያልተከተለ ነው፤ ሲሉ ይተቻሉ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የሒሳብ አያያዝ እና ፋይናንስ መምህሩ አቶ ታምራት መንገሻ በበኩላቸው፣ ባንኩ አሁንም፣ የደንበኞቹን እምነት ለማስጠበቅና ዝናውን መልሶ ለማግኘት በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ማተኮር እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት፣ ፈቃደኛ ሳይኾኑ በመቅረታቸው አልተሳካም፡፡

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።