የፒያሳ መፍረስ በነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ቅሬታ

Your browser doesn’t support HTML5

የፒያሳ መፍረስ በነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ቅሬታ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ፒያሳ አካባቢ፣ ከራስ መኮንን ድልድይ ጀምሮ፣ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ እስከሚጠራው ሰፈር ሰሞኑ እየተካሄደ ያለው የቤት ፈረሳ እና ፈረሳው እየተከናወነ ያለበት መንገድ በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎቹ እንዲነሱ የወሰነው አካባቢውን ለማልማት እቅድ በመያዙ መሆኑን ቢያስታውቅም፣ "ማንነታችንን ተነጥቀናል" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች እና የከተማ ልማት ባለሙያዎች፣ ፒያሳ አሮጌ ሰፈርም ቢሆን፣ የከተማዋን በርካታ ታሪኮች አቅፎ የያዘ በመሆኑ ልማቱ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ መካሄድ ነበረበት ሲሉ ይከራከራሉ።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)