የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና

በዩናይትድ ስቴትስ የቴክሳስ ግዛት ውስጥ፣ በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድምበር አቅራቢያ ሲበር የነበረ ሄሊኮፕተር የተከሰከሰበትን ስፍራ ባለስልጣናት ሲጎበኙ

በዩናይትድ ስቴትስ የሜክሲኮ ድንበር ሲቆጣጠር የነበረ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሁለት የብሔራዊ ጥበቃ ወታደሮች እና አንድ የአሜሪካ ድምበር ጠባቂ መሞታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ጥምር ግብረ ሃይል ባወጣው መግለጫ፣ ለፌደራል የደቡብ ምዕራብ ድንበር ጥበቃ ልዑካን ቡድን የተመደበው ዩ ኤች -72 የተሰኘው ሄሊኮፕተር አርብ እለት ከሰዓት የተከሰከሰው፣ ሪዮ ግራንዴ በተባለችው የቴክሳስ ከተማ አቅራቢያ የበረራ ስራ እያከናወነ ባለበት ወቅት ነው።

የሰሜኑ ጥምር ግብረኃይል በመግለጫው አንድ ሌላ አንድ ወታደርም ጉዳት እንደደረሰበት እና የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን አመልክቷል። የአካባቢውን ባለስልጣን ጠቅሶ የዘገበው አሶስዬትድ ፕሬስ። በሄሊኮፕተሩ ውስጥ አንድ ሴት እና ሦስት ወንዶች እንደነበሩ እና ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን አመልክቷል።

የብሔራዊ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ሆካንሰን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ፣ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች እና የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።