የሩሲያው ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ የቀብር ሥነ ስርዓት ተፈጸመ

  • ቪኦኤ ዜና

የሩሲያው ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ የቀብር ሥነ ስርዓት፣ ሞስኮ፤ ሩሲያ እአአ የካቲት መጋቢት 1/2024

ከሁለት ሳምንት በፊት በሩሲያ እስር ቤት ውስጥ ህይወቱ ያለፈው የሩሲያው ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ የቀብር ሥነስርዐት በከፍተኛ የፖሊስ ጥበቃ ሥር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ዛሬ ዓርብ ሞስኮ ውስጥ ተፈጸሟል፡፡

አስክሬኑን ወደ ቤተክርስቲያኑ ሲዘልቅ ከውጭ ይጠባበቁ የነበሩ ሰዎች በከፍተኛ ጭብጨባ በታጀበ ድምጽ “ናቫልኒ ናቫልኒ” በማለት ሲጮሁ ታይተዋል፡፡ የናልቫኒ ወላጆችና ሌሎች ሰዎች ከተከፈተው ሳጥን ውስጥ የነበረውን የናልቫኒን አስክሬን ሲደባብሱና ሲስሙ ተስተውለዋል፡፡

ከአጭር ጊዜ ከተካሄደው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤተክርስቲያኑ በመውጣት ሌላ ከፍተኛ የፖሊስ ኃይል ወደ ተሰማራበት የቦሪሶቮስኮይ መካነ መቃብር አምርተዋል፡፡

የሩሲያ ባለሥልጣናት እስካሁን የ47 ዓመቱ ናቫልኒ የሞተበትን ምክንያት አልገለጹም፡፡