ጥቁር ሴቶች በካንሰር በሦስት ዕጥፍ ይጠቃሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ጥቁር ሴቶች በካንሰር በሦስት ዕጥፍ ይጠቃሉ

ዋሺንግተን ዲሲ፣ ከመላው አገሪቱ ከፍ ያለ የጡት ካንሰር ሕሙማን የሚገኙባት ከተማ ናት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆኑቱ ጥቁር ሴቶች ናቸው።

ጥቁር ሴቶች፣ አስቀድሞ በመድኃኒት ሊታገሥ የማይችል “ትሪፕል ኔጌቲቭ” ለተሰኘ የካንሰር ዓይነት ተጋላጮች እንደሆኑ ጥናቶች ያመላክታሉ። በተጨማሪም ጥቁር ሴቶች፣ ገና ከለጋ ዕድሜያቸው አንሥቶ፣ በሰውነታቸው ውስጥ የካንሰር እድገት ሊጀመር እንደሚችል የሚገልጹ ባለሞያዎች፣ አስቀድመው ዓመታዊ ምርመራቸውን እንዲጀምሩ ያሳስባሉ።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው “ብረስት ኬር ዋሺንግተን ዲሲ” የተሰኝው ተቋም፣ በኑሮ ደረጃቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጥቁር ሴቶች፣ የጡት ምርመራ እንዲያገኙ እየሠራ ይገኛል።

በፒቢኤስ ጣቢያ የተጠናቀረውን ዘገባ፣ ኤደን ገረመው ወደ አማርኛ መልሳዋለች።