የልጆችን ማንነት አስጠብቆ የማሳደግ የዳያስፖራው ፈተና

Your browser doesn’t support HTML5

የልጆችን ማንነት አስጠብቆ የማሳደግ የዳያስፖራው ፈተና

በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከአገራቸው የሚወጡ ኢትዮጵያን ቁጥር እየጨመረ መኾኑ ሲገለጽ፣ በውጭ ተወልደው የሚያድጉ ልጆችም እንደሚበዙ ይታሰባል፡፡ ወላጆችም የመጡበትን ኢትዮጵያዊ ባህላዊ ዕሴትንና ሃይማኖታዊ አስተምህሮን በሚያንጸባርቅ መንገድ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ጥረት ማድረጋቸው አልቀረም።

ኾኖም ባለሞያዎች እንደሚሉት፣ ይህ ሁኔታ በአመዛኙ በወላጆች እና በልጆች መካከል ክፍተትን በመፍጠር ልጆችን እስከ ራስ ማጥፋት የሚያደርስ ድባቴ ውስጥ ይከታቸዋል።

ልጆችን በውጭ የሚያሳድጉ ወላጆች በሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ዘገባ አሰናድተናል።