የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ሥቃይ እያስከተሉ መሆኑ በእጅጉ እንዳሳሰበው የገለጸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብዳቤ የጻፉት፣ አገራቸው በኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአምባሳደሩ ስለተጻፈው ደብዳቤ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኤምባሲው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ኃላፊ ናዮሚ ፌሎውስ፣ በኢትዮጵያ ያሉት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ አገራቸው ጥረት እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡