ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ አሁንም ወረርሽኝ ሆኖ እንዳይከሰት ስጋት ፈጥሯል። በተለይ በወጣቶች ዘንድ የሚታየው የሱስ ተጋላጭነት መጨመር፣ የወሲብ ጓደኛ ማብዛት እና ለኤች አይ ቪ/ኤድስ ይሰጥ የነበረው ትኩረት መቀነስ ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የጤና ሚኒስትር አመልክቷል።
ቫይረሱ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ስላለው ስርጭት እና የመቆጣጠር እንቅስቃሴ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።