የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙርያ ወረዳ በሻራ ቀበሌ ባለፈው ነሐሴ ያልታጠቁ ሦስት ሰላማዊ ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጪ መገደላቸውን አስታወቀ።
በግጭቱ አጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ሰባት መኾናቸውንም የኢሰማኮ ሪጅን ዳይሬክተር እና የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል ኃላፊ ኢማድ አብዱልፈታህ ለአሜሪካ ድምፅ አታውቀዋል።
መንግሥት በሦስት ያልታጠቁ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ የሆነ ግድያ የፈጸሙ፥ በቁጥጥር ሥር በዋሉ ሰዎች ላይ ድብደባ የፈጸሙ እና ንብረት ያወደሙ የመንግሥት የጸጥታ አባላት እና ሌሎችም ሰዎች ላይ አስፈላጊ የሆነውን የተሟላ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥ አቶ ኢማድ አሳስበዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡