ከአደጋ የተረፍነው በአብራሪው ብቃት ነው - አንድ ተሳፋሪ
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የበረረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 106 አውሮፕላን፣ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርስ ቦታ ስቶ ማረፉን አየር መንገዱ አስታወቀ።
በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፋሪ ከነበሩት መንገደኞች አንዱ የኾኑት አቶ ገብረህይወት ወልደገብርኤል፣ አውሮፕላኑ ከመነሻው የተለየ ድምፅ አሰምቶ እንደነበር ገልፀዋል። የአውሮፕላኑ ግራ ጎማ ተቃጥሎ መመልከታቸውንም ተናግረዋል።
ኹኔታው አውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር የገለፁት እኚኹ ተሳፋሪ፣”ከፍተኛ ጩኸትም ነበር” ብለዋል። ተሳፋሪው “ከአደጋ የተረፍነው በአብራሪው ብቃት ነው” ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡