የመብት ተቋማት በተማሪዎች የወሊድ ፈቃድ ላይ የወጣው መመሪያ እንዲነሳ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የመብት ተቋማት በተማሪዎች የወሊድ ፈቃድ ላይ የወጣው መመሪያ እንዲነሳ ጠየቁ

የትምህርት ሚኒስትር፣ አንዲት ተማሪ በወሊድ ምክንያት 16 ቀናት እና ከዛ በላይ ከትምህርት ገበታዋ ላይ ከቀረች ከዘመኑ ትምህርት ትታገዳለች በሚል በቅርቡ ያወጣውን ረቂቅ መመሪያ ተቃውመው አስር የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መግለጫ አውጥተዋል። ረቂቅ መመሪያው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን አወንታዊ ድንጋጌዎች የሚንድና የሴቶችን መሠረታዊ የመማር መብቶች በግልፅ የሚነፍግ ነው ሲሉም ረቂቅ መመሪያ በድጋሚ እንዲታይ ጠይቀዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)