በሰሜን ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች አራት ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች አራት ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ

በዐማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በሦስት ወረዳዎች፣ በ2015/16 መኸር ምርት የተከሠተው ድርቅ ባስከተለው ረኀብ፣ አራት ተጨማሪ ሰዎች እንደሞቱ፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

በዞኑ በጃን አሞራ፣ በየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች፣ ድርቁ ባስከተለው ጉዳት፣ ከወር በፊት 32 ሰዎች እንደሞቱ፣ በአካባቢው ባለሥልጣናት ተገልጾ እንደነበር ዩኒቨርሲቲው አስታውሷል፡፡ ተቋሙ በራሱ፣ ከአንድ ወር በላይ አደረግኹት ባለው ጥናት ደግሞ፣ ሕይወታቸው ያለፉት ወገኖች ቁጥር ወደ 36 ከፍ እንዳለና ከ72ሺሕ በላይ እንስሳትም እንደሞቱ፣ መምህር እና የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ አበጀ፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በሦስቱ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 37 ቀበሌዎች፣ ከ107ሺሕ በላይ ሰዎች፣ አስቸኳይ የዕለት ምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ እስከ አኹን የደረሰው ርዳታ በቂ እንዳልኾነ የተናገሩት የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ፣ በመኸሩ ምንም ዐይነት ምርት ባለመገኘቱና እንስሳቱም በመሞታቸው፣ ነዋሪዎቹ ከዓመት እስከ ዓመት ርዳታ እንደሚያሻቸው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።