እንግሊዝ ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞች በሩዋንዳ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ለማድረግ ጥረቷን ቀጥላለች።
በሩዋንዳ ስርዓት ላይ ያለውን ስጋት ለማስወገድም፣ እንግሊዝ ጠበቆቿን በሩዋንዳ ፍርድቤቶች እንደምትመድብ አስታውቃለች።
የእንግሊዝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል መንግስት ስደተኞችን ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ለመላክ ያቀረበውን እቅድ ህገወጥ ነው በማለት ውሳኔ ያሳለፈ ቢሆንም፣ አንዳንድ ፖለቲከኞች የሩዋንዳ እቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ አዲስ መንገድ ለመንደፍ ከመሞከር ግን አላገዳቸውም።
የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጀምስ ክሌቨርሊ በዚህ ሳምንት ወደ ሩዋንዳ በመብረር፣ የጥገኝነት ሂደት አቅሟን ለማስፋት ለሩዋንዳ ተጨማሪ 15 ሚሊየን የሚከፍል ስምምነት እንደሚፈራረሙ ሰንዴይ ታይምስ የተሰነው ሚዲያ ዘግቧል።
እ.አ.አ በ2020 ስራ ላይ ሊውል ታስቦ ለነበረው የጥገኝነት እቅድ፣ ሩዋንዳ 140 ሚሊዮን ዩሮ ከብሪታኒያ ተቀብላ የነበረ ሲሆን፣ እቅዱ ተግባራዊ ሊሆን ጥቂት ቀናት ሲቀረው ባጋጠመው ህጋዊ ተግዳሮቶች ተስተጓጉሏል።
በእቅዱ የፀናው የእንግሊዝ መንግስት ግን ከአፍሪካዊቷ ሀገር ጋር መደበኛ ስምምነት ለመፈራረም ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።