የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የአካባቢ ጥበቃ ጥረት ተከበረ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የአካባቢ ጥበቃ ጥረት ተከበረ

ዛሬ በዱባይ በተጀመረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ከኾኑ የኢትዮጵያ ተቋማት መካከል አንዷ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት።

ቤተ ክርስቲያኒቱ፣ ሀገር በቀል የደን ሀብት ለትውልድ እንዲተላለፍ ለዓመታት የሠራች የብዝኀ ሕይወት ማዕከል ኾና ቆይታለች።

በብዙ ሺሕ ሄክታር የሚገመት የኢትዮጵያ መሬት ርቃኑን እንዳይቀር ማድረጓን፣ ከትልቅ ስኬት የቆጠረው “አክት አሊያንስ” የተሰኘ የተቋማት ኅብረም፣ ከሰሞኑ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የዘመናት ጥረት ዕውቅና ሰጥቷል።

የሽልማቱን ፋይዳ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን የደን ልማት ሥራዎች ይዘት ለመቃኘት፣ ሀብታሙ ሥዩም አቶ ተዋነይ ሰይፈ ሥላሴን ጋብዟል።

ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።