በየዓመቱ ኅዳር 21 ቀን፣ በርእሰ ገዳማት ወአድባራት አኵስም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን የሚከበረው የጽዮን ማርያም በዓል፣ ከአራት ዓመታት መታጎል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት፣ ዛሬ ተከብሮ ውሏል፡፡
ከዓመታት መስተጓጎል በኋላ፣ በዓሉን ለማክበር የቻልነው፣ “ሰላም በመስፈኑ ነው፤” ያሉት የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች፣ የሰላም ይዞታው እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡
በዛሬው የበዓል አከባበር ላይ፣ ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ የአኵስም ጽዮን ተሳላሚዎች ታድመዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።