አወዛጋቢ እና ስመጥር የአሜሪካ የፖለቲካ መሪ ህይወት እና ትተውት ያለፉት ቅርስ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

አወዛጋቢ እና ስመጥር የአሜሪካ የፖለቲካ መሪ ህይወት እና ትተውት ያለፉት ቅርስ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሄንሪ ኪሲንጀር አረፉ፡፡

በቀድሞው ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን ዘመነ መንግሥት ከነበራቸው ኃላፊነት ከተሰናበቱም በኋላ በዐለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖአቸው የቀጠለው ኪሲንጀር በመኖሪያቸው በከኒቲከት ግዛት ያረፉት በአንድ መቶ ዓመታቸው ነው፡፡

ዜና ዕረፍታቸውን የተናገረው የአማካሪ ተቋማቸው ሲሆን የሕልፈታቸው ምክንያት ግን አልተገለጸም፡፡

የአሜሪካ ድምጽዋና ዲፖሎማሲ ጉዳዮች ዋና ዘጋቢ ሲንዲ ሴን ባጠናቀረችው ዘገባ የእኒህን አወዛጋቢ እና እጅግ ስመጥር የአሜሪካ የፖለቲካ መሪ ህይወት እና ትተውት ያለፉትን ቅርስ ትዳስሳለች፡፡

ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡