በትግራይ በጦርነቱ የተቋረጠ የወራት ደመወዝ ባለመከፈሉ የሠራተኞች ተነሣሽነት እንደተጎዳ ኢሰመኮ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ በጦርነቱ የተቋረጠ የወራት ደመወዝ ባለመከፈሉ የሠራተኞች ተነሣሽነት እንደተጎዳ ኢሰመኮ ገለጸ

በትግራይ ክልል፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረ የመንግሥት ሠራተኞች የ18 ወራት ደመወዝ እስከ አሁን እንዳልተከፈለ የጠቀሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሥራ ተነሣሽነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ፣ በክልሉ ማረሚያ ቤቶች፣ የፖሊስ ጣቢያዎች እና የጤና ተቋማት ላይ ባደረገው ክትትል፣ የሠራተኞች የሥራ ተነሣሽነት እንደተጎዳና በዚኽም ሳቢያ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ክፍተት እና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ችግሮችን ማስተዋሉን፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ በኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ክፍል ዲሬክተር ሰላማዊት ግርማይ፣ ኮሚሽኑ፣ የክትትሉን ሙሉ ሪፖርት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

በተቋማቱ ውስጥ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት፣ የፌዴራል መንግሥት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በትኩረት እንዲሠሩም፣ ዲሬክተሯ አክለው አሳስበዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።