የፓርላማ አባላቱ የታንዛኒያው ድርድር ሒደት ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጽ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የፓርላማ አባላቱ የታንዛኒያው ድርድር ሒደት ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጽ ጠየቁ

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በታንዛኒያ ያደረጉት የሰላም ድርድር ሒደት ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጽ፣ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

ያለስምምነት የተቋረጠውን ድርድር አስመልክቶ፣ የአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው ሦስት የምክር ቤቱ አባላት፣ በቀጠለው ግጭት ሳቢያ ወደየአካባቢያቸው ተመልሰው የመረጣቸውን ሕዝብ ማነጋገር እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ሁለቱም አካላት ያልተስማሙባቸውን ጉዳዮች፣ በግጭታቸው እየተቸገረ ሰላም ለናፈቀው ሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉና ድርድሩን እንዲቀጥሉ፣ የምክር ቤት አባላቱ አሳስበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።